እድገት እየተፈጠረ ነው።

፨፨፨፨፨/////////፨፨፨፨፨

የመውደቅ ስሜት ሲሰማህ፣

አንገትህን በደፋህ ጊዜ፣

በተሰበርክ ወቅት፣ 

ተስፋ በራቀህ ቅፅበት፣

አዎ! ያኔ እድገት እየተፈጠረ ነው።

ያኔ ለውጥ እየመጣ ነው።

ያኔ አዲስ ነገር እዳደረክ ይሰማህ።

አዎ! ጀግናዬ..! የወደከው ስለጀመርክ፣ ስለሞከርክ ነው፤ የቆመ፣ ያልጀመር፣ ካለበት ያልተንቀሳቀሰ እንዴትም ሊወድቅ አይችልም።

አንገትህን የደፋሀው፣ ተግባርህ ያሰብከውን ስላላስገኘልህ ወይም እንዳሰብከው ሳትጀምር ስለቀረህ ነው፤ የመጀመር፣ የማድረግ ሃሳብ የሌላቸው፣ ያልጀመሩ አንገታቸውን የሚደፉበት ምክንያት የላቸውም። They are already obsessed with being stable. በመቆም የታሰሩና የተመቻቹ ናቸው።

የተሰበርከው የምትጠብቀው ትልቅ ውጤት ስላለ ነው፤ ያልጀመረን፣ የቆመን ሄዶ የሚሰብረው ምንም ነገር የለም።

ተስፋ የሚርቅህ ትልቅ ተስፋ ስለነበረህ ነው፣ ነገን የማያይ፣ ተስፋ የማያደርግ፣ የተሻለውን የማያልም ሰው ዛሬ የሚርቀው ትናንት ተስፋ ያደረገው፣ የሚመኘው ነገር የለውም።

አዎ! የእድገትህ፣ ቀና የማለትህ፣ የከፍታህ መሰረት ሃሳብ፣ ምኞት፣ ተስፋ፣ ህልም ናቸው። እነዚህን ካለህ ማደግ ጀምረሃል፣ ለውጥ ላይ ነህ።

የእድገት ሃሳብ ሳይኖር እድገት አይጠጋህም፤

የለውጥ ጥልቅ መኞት ከሌለህ መቼም አትቀየርም፤ ለእርምጃ የሚጋብዝህ፣ ውስጥህን የሚነካ ጠለቅ ያለ ምኞት ያስፈልግሃል።

ተስፋ ከሌለህ ምንም አታገኝም፣ ህይወት ጠዓም አትሰጥህም፣ ዛሬን አትኖርም ነገን አታልምም።

ሃሳብ፣ ጥልቅ ምኞት፣ ተስፋ ከሌለህ ህልምህን ኬትም አታመጣውም፤ የትግልህን መጨረሻ አታውቀውም፤

መሔጂያህ፣ መዳረሻህ፣ ማረፊያህ የተ እንደሆነ ሃሳቡ አይኖርህም። እንደ ማንኛውም ህልም እንደሌለው ሰው፣ ህይወት ባዘጋጀችልህ ጎዳና ትመላለሳለህ፣ የት እንደምትሔድ አታውቅም፣ መቼ እንደምትደርስ አታውቅም፣ ሌላ ቀጣይ ጉዙ ይኑርህ አይኑር የምታውቀው ጉዳይ የለም፤ እንደፈለገች የምትሾርህ ህይወት እራሷ ትሆናለች።

አዎ! ጀግናዬ..! ሃሳብ፣ ጥልቅ ምኞት፣ ተስፋ፣ ህልም ካለህ ስለሚፈጀው ጊዜ አታስብ ሁሉም በጥረትህ ልክ በቅርቡ ይሳካል።

አንተ ብቻ ብትወድቅም ድጋሜ ተነስ፤

ብትሰበርም እራስህን ጠግን፤

አንገትህን ብትደፋም በተግባርህ ቀና በል፤

ተስፋ ቢርቅህም አንተ ተጠጋው ሁሌም ለተሻለ ነገር ተስፋ እንዳለ አስብ።

ውብ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅

ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋