በኢኮኖሚክስ ፍፁም ትክክል የሚባል ሃሳብ የለም
በኢኮኖሚክስ #ፍፁም ትክክል የሚባል ሃሳብ የለም!
#ቀላል_ምሳሌ፦ የዋጋ ንረት የመፍትሄ ሃሳቦች የተለያዩ ናቸው! ለአንዱ ሀገር የሰራ የመፍትሄ ሃሳብ ለሌላ ሀገር የዋጋ ንረት አባባሽ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ተመሳሳይ የዋጋ ንረት የመነሻ ምክንያት (ከፍላጎት መጨመር/Demand Pull አልያም የማምረት ወጪ መጨመር/Cost Push) ቢፈጠር እና የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እውቀት ያላቸው ሰዎች የሚከተለውን ምክር ቢለግሱ.......
#የምጣኔ_ሃብት_ባለሙያ1፦ "በገበያ የገንዘብ ስርጭት እንዲጨምር ማድረግ #ከፍላጎት በሚነሳ ምክንያት አንፃር የዋጋ ንረትን ያባባብሳል! ስለዚህ የገንዘብ አቅርቦትን በመቀነስ የዋጋ ንረቱን መቀነስ ይቻላል" የሚል ምክረ ሃሳብ ቢያቀርብ።
#የምጣኔ_ሃብት_ባለሙያ2፦ በተቃራኒው "ለአምራች ሃይሉ የገንዘብ አቅርቦትን በማሳደግ #የማምረት አቅም/የግብዓት አቅርቦት እንዲሻሻል በማድረግ አቅርቦትን በመጨመር የዋጋ ንረት እንዲቀንስ ማድረግ ይቻላል" የሚል ምክረ ሃሳብ ቢያቀርብ።
የሁለቱም ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብ በመርህ ደረጃ ስህተት የለበትም! ማንኛቸውም ባለሙያ የሰጠሁት የመፍትሔ ሃሳብ ፍፁም ትክክለኛውን ነው በሚል መኩራራትም አይችልም! የመፍትሔ ሃሳቦች ሲተገበሩ የመንሻፈፍ አጋጣሚዎቻቸው ብዙ ናቸው። ለዚህ ነው ታዋቂ የኢኮኖሚክስ Assumption መላምቶች (Other Things Remaining Constant) በሚል የሚጀምሩት።
#ለምሳሌ፦ በ1930 በአሜሪካ የተከሰተው ኢኮኖሚያዊ ቀውስ (Great Depression) በዋናነት መነሻው ምክንያት የአምራች ክፍሉ ያመረተውን ከፍተኛ መጠን ምርት መግዛት የሚገባው የሸማች ክፍሉ በበቂ ሁኔታ መሸመት ባለመቻሉ አምራቾች የተመረቱ ምርቶች ገበያ ካጡ ተጨማሪ ምርት ከማምረት በመቆጠብ ሰራተኛ በማሰናበታቸው በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛው የስራ አጥነት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል።
#ለምሳሌ፦ በአሜሪካ በ1929 ስራ አጥነቱ 3.2% ነበር፤ በዓመቱ 6 ሚሊየን አሜሪካዊያን ስራ በማጣታቸው በ1930 የስራ አጥነቱ ቁጥር 19.4% ደረሰ በ1933 ስራ አጥነቱ 25% አልፎ ነበር፡፡
ይህ ችግር እንዲቀረፍ ብዙ ኢኮኖሚስቶች ተሞክረው በመጨረሻ እንግሊዛዊው ኢኮኖሚስት ጆን ሜሬድ ኬነስ "የገንዘብ አቅርቦትን ባለመቀነስ የሸማች ክፍሉን አቅም በማሳደግ ችግሩን መቅረፍ ይቻላል" የሚለው ሃሳብ በLogic አደገኛ በመሆኑ ከብዙ ክርክር በኋላ "እስቲ ይሞከር!" በሚል ነበር የተተገበረው! ነገር ግን ችግሩ ለመቀረፍ 10ዓመት ቢፈጅም ምክረ ሃሳቡ መፍትሄ መሆን በመቻሉ መማሪያ ሆኖ Keynesian Theory በሚል ተመዝግቧል።
በወቅቱ ከኬይነስ በፊት ከቀረቡ የመፍትሄ ሃሳቦች መካከል "የሰራተኛውን ክፍያን በመቀነስ እና የአምራች ክፍሉ የሚከፍለውን የወለድ መጠን በመቀነስ ወጪን በመቆጠብ ስራ አጥነቱ እናዲቃለል ማድረግ ይቻላል" የሚለው ሲሆን ኬይነስ በበኩሉ "የሰራተኛውን ክፍያ ከመቀነሰ ይልቅ የሰራተኛው ክፍል የመሸመት አቅም እንዲጨምር በማድረግ ሸማች እንዲሆን ማድረግ ይቻላል"፤ ይህንን ተከትሎ የአምራች ክፍሉ የማምረት መጠን እየጨመረ ይሄዳል የሚል ነበር፡፡ በተግባርም አስተሳሰቡ ውጤት አምጥቷል፡፡
በሀገራችን ኢኮኖሚክስን የተማሩ ሰዎች በአብዛኛው ለጊዚያዊ ችግሮች የመፍትሄ ሃሳብ እና የኢኮኖሚያዊ ችግሮች መነሻ ምክንያትን ሲያስቀምጡ ሃሳቦቹ የተለያዩ ናቸው። ይህ ማለት ባለሙያዎቹ ሙሉ ለሙሉ ስህተቶች ናቸው እና ትክክለኛው መፍትሄ እና ምክንያት የቱ እንደሆነ አልታወቀም አያስብልም።
አስር የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ኢትዮጵያ ለምን የከፋ ድህነት ውስጥ ለመኖር ተገደደች? ተብለው ቢጠየቁ። ስምንት አልያም አስር የተለያዩ ምክንያቶችን ሊያቀርቡ ይችላሉ። ስለዚህ ኢትዮጵያ ከድህነት እንድትወጣ ምን ይደረግ? ቢባሉም ስምንት አልያም አስር የተለያዩ ከችግር መውጫ መንገዶችን በምክንያትነት ሊያቀርቡ ይችላሉ።
ለዚህ አይነቱ ችግር የባለሙያዎች ስብስብ በመፍጠር የሃሳቦችን እድል እና ስጋት በመወያየት ወደ ዋና መሰረታዊ (Significant) ነጥብ እንዲደርሱ ማድረግ ይቻላል! ደግሞም መንግስታት ይህንን ዘዴ ይጠቀማሉ።
#ለምሳሌ፦ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ቤት ውስጥ ያሉ ኢኮኖሚስቶች የጥሬ ገንዘብ ገደብ ይቀመጥ! የሚለው ውሳኔ ላይ በተናጥል የተለያየ ምልከታ እንደሚኖራቸው እገምታለሁ። ነገር ግን እንደማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳዳሪነታቸው በጋራ ከየልዩነታቸው ወደ ተመሳሳይ ውሳኔ እንደደረሱ መገመት ይቻላል። በተመሳሳይ የገንዘብ ሚኒስትር፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ አማካሪ ቡድኑ፤ ወዘተ ውስጥ በምክንያት እና መፍትሄ ላይ የሚኖረው ሁኔታ በተናጥል እና በቡድን ሃሳቦቻቸው የተለያዩ ነው የሚሆኑት።
በሀገራችን ብዙ ሰዎች ኢኮኖሚክስን በብዙ ጥልቀት በትምህርት እና በስራ ልምድ እንደሚያውቁት ግልፅ ነው! ስለዚህ የሚሰማቸውን ስሜት ለማጋራት ግዴታ ጥቂት ሰዎች ብቻ በየቀኑ የሚያቀርቡትን ሚዲያዎች መፈለግ አይጠበቅባቸውም፤ ሃሳቦቻቸው ለፖሊሲ አውጪዎች እንዲደርስ መፈለግ የለባቸውም፤ ሃሳቦች ትክክል እና ስህተት መሆናቸውን የሚመዝን አካል ስለመኖሩ ማሰብ የለባቸውም፤ ወዘተ። ስለዚህ የተማሩትን እና የሚያውቁትን ብቻ ያንጸባርቃሉ፡፡
#ለምሳሌ፦ በሀገራችንን የምጣኔ ሃብት ዙሪያ አስተያየት ለመስጠት በተለያዩ ሚዲያዎች የሚቀርቡት እንዲሁም ሚዲያዎች የሚያቀርቧቸው ሰዎች ጥቂት እና ተመሳሳይ ናቸው (ከጥቂት ጊዚያት ወዲህ እኔንም ይጨምራል!) ይህ ሁኔታ የሃሳብ ተዋፅኦን ይቀንሳል!
#ለምሳሌ፦ እኔ በ2019 በፌስቡክ የማውቀውን የኢኮኖሚ ፅንሰ ሃሳብ መፃፍ የጀመርኩት በኮመን ሴንስ ኢኮኖሚያዊ ሃሳቦችን ለመረዳት እድል ለሌላቸው ሰዎች ለማጋራት ነው። አሁንም የማደርገው ይህንኑ ነው። ልኩን ሳይሆን ልክ ነው ብዬ የማምንበትን እና የማውቀውን ሃሳብ ብቻ ነው የማጋራው!
ስለዚህ ሀገር ኢኮኖሚክስን ያስተማረቻቸውን እንዲሁም በራሳቸው ያዳበሩትን እውቀት ባገኙት አጋጣሚ (በማህበራዊ ሚዲያ፤ በህትመት ሚዲያ፤ በራዲዮ፤ በቲቪ፤ ወዘተ) ማጋራት ተገቢ ነው። ኢኮኖሚያዊ መረጃ እና ሃሳብ ለመንግስት፤ ለሚዲያዎች፤ ለተማሪዎች፤ ለመደበኛው ሰው፤ ወዘተ በጣም አስፈላጊ ነው።
Post a Comment
0 Comments