💛ደግነት የእውነተኛ ፍቅር የተፈጥሮ ውበታችን ነው።በሕይወት ጉዞ ላይ በቂ የሆነ ስንቃችን ነው።ትዕቢት ና ኩራት የምናጠፋበት ልዩ ኃይላችን ነው።

💜ከትሕትና የበለጠ መልካም ነገር የለም። ሌሎችን መረዳት የመጀመርያው ንቃት እና ዕውቀት ነው፣ መንፈሳችንንም ወደ ላይ ክፍ ከፍ ያደርገዋል።

💛ልግስና የነፍስ ምግብ ነውና
፣ ለሚሰጥ አብዝቶ ይመለስለታል።
ጥሩ እርካታ ያገኘ ጥሩ ክፍያ እንዳገኘ ነው ። ባለንና በምናገኘው ነገር ኑሯችንን ስንመሰረት በምንሰጠው ነገር ደግሞ ሕይወታችንን እንመሰርታለን ። ለራሳችን ማድረግ የምንችለው ትልቁ ነገር ቢኖር ለሌሎች ጥቂት ነገር ማድረግ መቻል ነው ።

🔑መስጠት እውነተኛ የደስታ መገለጫ ነውና፣የሕይወትህ መሰረት አድርገው !