🌓የአጋጣሚ ትንሽ የለውም፤

✨የአጋጣሚ ትንሽ የለውም፤
ህይወት በክስተቶች የተሞላች ነች። የክስተቱ ባለቤት ማንም ይሁን ማንም፣ የክስተቱ ተቀባይ ግን አንተ ልትሆን ትችላለህ። አንድ ነገር ሲመጣብህና ሲመጣልህ አንድ አይነት ምላሽ አትሰጥም።

💫የመጣብህን እንዳመጣጡ ትመልሳለህ፣ የመጣለህን ግን በአግባቡ ትቀበለዋለህ፣ ትጠቀመዋለህ። ለዚህም የዘወትር ዝግጁነትህ ወሳኝ ነው። በህይወትህ የሚመጡልህ መልካም አጋጣሚዎች ህይወትህን እስከ ወዲያኛው የመቀየር ሃይል አላቸው። መቼም እስከ ዛሬ ስንት አጋጣሚዎችን እንዳሳለፍክ፣ እንዳባከንክ አንተ ታውቃለህ፤ ለሚቀጥሉት ድንቅ አጋጣሚዎች ግን በፍፁም ሳይጠቅሙህ እንዲያልፋ መፍቀድ የለብህም። አዎ! እራስህን በብዙ ማዘጋጀት ይኖርብሃል።
ጊዜና አጋጣሚ አንድ ናቸው አብረው ይመጣሉ፤ አብረውም ላይመለሱ ይሔዳሉ።

🌓አዎ! አንዳች ነገር እንዳያመልጥህ ዘወትር ተዘጋጅተህ ጠብቅ።ከተጠቀምክበት ዓለም መጥፎና ከባድ ገፅ ብቻ ሳይሆን ቀላል ብልሃትህንና ዝግጁነትህን  የሚሹ ብዙ የህይወት በረከቶች አሏት፤ ዋናው ያንተ በተገቢው ሰዓት፣
በትክክለኛው ቦታ፣ በተገቢው አኳሃን የተገኘውን አድል፣ አጋጣሚ ሳያመነቱ ተጠቅሞ መገኘት ነው።


 

Post a Comment

0 Comments